ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዲፕሎማቶች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በተለያዩ ሃገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር እየተወያዩ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተለያዩ ሃገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር እየተወያዩ ነው።

ውይይቱ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፣ የሚመደቡበትን ሃገር ፖሊሲ የመገንዘብና በሃገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብት የማስጠበቅ ሚና እንዳላቸውም አስታውሰዋል።

ውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የተደረጉ ለውጦችን ለመገምገም ያቀደ ነው።

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*