በአማራና በቅማንት መካከል ግጭት ተባብሷል ተባለ

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር በአማራና በቅማንት መካከል ትናንትና ዛሬ ተባብሷል የተባለውን ግጭት ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት መተማ መግባቱን የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ቢሮና መከላከያ አስታወቀ።

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ
በሁለት ቀናት ግጭትና የእርስ በእርስ ጥቃት ሰዎች መገደላቸውንና ቤቶች መቃጠላቸውን ሁለቱም አካላት አስታውቀዋል። የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እስካሁን በቁጥር የተጣራ መረጃ የለም ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ ማክሰኞ ዕለት በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃና ኮኪት መከላከያ በወሰደው ከመጠን ያለፈ እርምጃ አንድ ታዳጊን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውንና 18 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል ፀጥታ ቢሮ አታውቋል። መከላከያ ደግሞ ፤ አድፍጦ የታጠቀ ኃይል ወደ ሠራዊቱ በመተኮሱ ምክኒያት ሠራዊቱ እራሱን ሲከላከል እንደነበር ገልፆ “የማን ጥይት ማንን እንደመታ ገና አልተረጋገጠም” ብሏል።

ጽዮን ግርማ የአማራ ክልል የሰላም ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌና የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታ ማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ) https://av.voanews.com/clips/VAM/2019/01/11/f8aa7bc1-2d4d-4ed3-9b2f-972306d7c3b2_32k.mp3?download=1

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*